
ዎልቭስ የ2025/26 የውድድር ዘመን ቅድመ እይታ
ውልቭስ የመውረድ ስጋት እንዳይደርስባቸው ተስፋ በማድረግ ቀጣዩን የፕሪሚየር ሊግ ወቅትን ለመቀበል እየተዘጋጁ ነው።
ባለፈው ዓመት ከመዉረድ ለጥቂት ነበር የተረፉት አሰልኝ ቪቶር ፔሬራ ከአስከፊዉ የወልቭሰ አጀማመር በኋላ ቡድኑን ተቀብሎ
በማርች ላይ ከመዉረድ ስጋት ሊያድናቸው ችሏል።
በጥንቃቄ ወደፊት መመልከት

ቡድኑ ምንም እንኳን ባለፈው የዉድድር ዘመን ቁልፉ ተጫዋቻቸው ማቲየስ ኩንያ ለተወሰነ ጊዜ በቅጣት ከሜዳ ቢርቅም ያለሱ
ማሸነፍ እንደሚችል አሳይቷል። አንድሬ እና ጆአአን ጎሜስ — ሁለቱም ጠንካራ የአማካይ ተጫዋቾች — በቡድኑ ውስጥ አሁንም
አሉ። ነገር ግን፣ ዮርገን ስትራንድ ላርሰን ባለፈው ዓመት ያበረከተውን የ14 ግብ አስተዋዕኦ ለመድገም ትልቅ ጫና ይጠብቀዋል።
ነገር ግን፣ ኩንያ፣ ራያን አይት-ኑሪ እና ኔልሰን ሴሜዶ ከቡድኑ በመልቃቸው በአሁኑ የዉድድር ዘመን ቡድኑ የዝግጅት ማነስ
ያለበት ይመስላል። እነዚህ ሶስቱ ተጫዋቾች ባለፈው የውድድር ዘመን ለውልቭስ የግብ አስተዋጽኦ ትልቁን ሚና የተጫወቱ
ተጫዋቾች ሲሆኑ በዚ የውድድር ዘመን ግን በቡድኑ ዉስጥ የሉም።
ዎልቭስ የሚያስፈልገው ነገር
ፔሬራ ተጨማሪ ፊርማዎችን ይፈልጋል፡ የሴሜዶን ቦታ ተረክቦ የሚጫወት የቀኝ ክንፍ ተከላካይ እና ከቡድኑ በወጡ ተጫዋቾች
ምክንያት የሚነሱ ክፍተቶችን ለመሙላት፣ አዲስ አጥቂ እና አማካኝ ይፈልጋል። እንዲሁም ፈጣን ተጽዕኖ እንደሚያሳድር
በማሰብ የፍሉሚኔዝ ተለዋዋጭ የክንፍ ተጫዋች የሆነውን ጆን አሪያን ለማምጣት አስቧል።

ከሜዳ ውጪም ያለውም ጉዳይ አስፈላጊ ነው
ደጋፊዎቸ በክለቡ አቅጣጫ ግራ ተጋብተዋል። በተለይም ክለቡ በፕሪሚየር ሊግ ስምንተኛ ተከታታይ የውድድር ዘመን መሳተፉን
ተከትሎ ባለቤቱ ፎሱን የተሻለ ስኬትን ለመሻት መነሳሳት ያንሳቸዋል በሚል ተጨንቀዋል። ያለ ድሎች የቅድመ ውድድር ጊዜው
ማለፉ ደሞ ደጋፊው እንዲረጋጋ አላረገም።
በብሩህ ጎኑ እንደሚታየው ዎልቭስ በቅርብ ጊዜ አዲስ “የእግር ኳስ አመራር ቡድን” ሰርቷል፣ ይህም በስፖርት ዳይሬክተር ዶሜኒኮ
ቴቲ ይመራል። ቴቲ ከፔሬይራ ጋር በሳውዲ አረቢያ ከነበረው ጊዜ ጀምሮ ይታወቃሉ። ቡድኑ የተረጋጋ የገንዘብ ሁኔታ ላይ
ይመስላል፣ እንዲሁም የስቲቭ ቡል ስታንድ ስታዲየም ከመልካም አገልግሎት መስጫ አካባቢዎች ጋር እንዲታደስ ስራዎች
እየተዘጋጁ ነው።
ታዳጊ ተሠጥኦ
ቡድኑ ተስፋ አስገኝቷል። ከሴልታ ቪጎ የፈረመው 21 ዓመት የሆነው የአጥቂ አማካይ ፌር ሎፔዝ፣ በላ ሊጋ ውስጥ አጭር ጊዜ
ብቻ ቢቆይም እንደ ቀጣዩ ታላቅ ተሰጥዖ ያለው ተጫዋች ይታያል።
ሌላው አስደሳች ስም ማቴዎስ ማኔ ነው፣ ያለፈው ወቅት ለዎልቭስ ከ18 በታች ቡድን ሰባት ጎሎች እና አራት ለግብ የሚሆኑ
ኳሶችን አመቻችቶ ያቀበለ ተጫዋች ነው። እሱ ወደ ዋናው ቡድን በፍጥነት አድጓል እና በዚህ የዉድድር ዘመን አስፈላጊ ሚና
ሊጫወት ይችላል።

የሚጠበቁ ተጫዋቾች
ከማርች 2022 ጀምሮ ያልጫወተው ኪ-ጃና ሆቨር፣ በቅድመ ውድድር ጊዜ ባሳየው አስደማሚ አቋም እንደ ቀኝ የክንፍ ተከላካይ
(ዊንግ ባክ) ለመጀመር ዝግጁ ይመስላል። ከብዙ የዉሰት ውል በኋላ ራሱን ለማሳየት ዕድሉ አለዉ።
ሳሳ ካላይድዝ፣ ከጉዳት እያገገመ ያለው ረጅሙ አጥቂ ወደ ጨዋታ ተመልሶ የማጥቃት እንቅስቃሴ ላይ ጥልቀት ሊጨምር
ይችላል።
ትንበያ
ከበርካታ የለቀቁ ተጫዋቾች እና ቡድኑን ካልተላመዱ አዲስ ፈራሚዎች አንፃር ዉሎቭስ ሌላ ከባድ የውድድር ዘመን
የሚገጥማቸው ይመስላል። በአማካይ ተንታኞች ከመውረድ ዞን በላይ 16ኛ ቦታን ይዘው እንደሚጨርሱ ይጠብቃሉ።
ወጣት ተጫዋቾቻቸውን በፍጥነት ከፔሬራ በቴክኒካዊ ተሞክሮ ጋር ማዋሀድ ከቻሉ በደረጃ ሰንጠረጁ ወደ መሀል መቀመጥ
ይችላሉ። ነገር ግን በተጨባጭ እይታ 17ኛ ደረጃን በመያዝ እንደገና በሊጉ የሚቆዩ ይመስላል።