የሁሉም ኳስ ግጥሚያዎችሌሎች ሊጐችፕሪሚየር ሊግ

ሴሜንዮ በድጋሚ ሲያስቆጥር ማንችስተር ሲቲ በኒውካስል ላይ የበላይነት አግኝቷል

ሲቲ የግማሽ ፍፃሜውን ዕድል አጥብቆ ይዟል

ማንችስተር ሲቲ የዋንጫው ባለቤት በሆነው ኒውካስል ላይ 2 ለ 0 በሆነ ከሜዳው ውጪ ድል በመቀዳጀት፣ ወደ ሌላ የካራባኦ ካፕ ፍፃሜ ለመድረስ አንድ እርምጃ ተቃርቧል። በአዲሱ ክለቡ ጥሩ አጀማመር ያደረገው አንዋን ሴሜንዮ በተከታታይ ለሁለተኛ ጨዋታ ግብ ማስቆጠር የቻለ ሲሆን፣ ራያን ቸርኪ ደግሞ በመጨረሻ ደቂቃ አስደናቂ ግብ በመጨመር ድሉን አረጋግጧል።

ይህ ውጤት ለፔፕ ጋርዲዮላ ቡድን የካቲት 4 በኢቲሀድ ስታዲየም ለሚደረገው የመልስ ጨዋታ ትልቅ ብልጫ ሰጥቷቸዋል። ኒውካስትል ዋንጫውን ለማቆየት ያላቸውን ተስፋውን ለማለምለም በመልሱ ጨዋታ እጅግ ከባድ ፈተና ይጠብቀዋል።

ኒውካስል ቀድመው ያገኟቸውን ዕድሎች አባክነዋል

ኒውካስል ጨዋታውን በጥሩ መነሳሳት የጀመረ ሲሆን፣ ገና በአምስት ደቂቃ ውስጥ መሪ መሆን ይገባው ነበር። አንቶኒ ጎርደን ቀደም ብሎ ያቀበለው ኳስ ጃኮብ መርፊን በቀኝ መስመር ነፃ ያወጣው ሲሆን፣ እሱ ያሻገረውን ኳስ ዮአን ዊሳ ክፍት ቦታ ላይ ሆኖ ቢያገኘውም፣ አጥቂው ግን ያንን ተስፋ ሰጪ ዕድል ሳይጠቀምበት ኳሱን ከግቡ አግዳሚ በላይ አውጥቷታል።

ሲቲ ቀስ በቀስ ጨዋታውን በመቆጣጠር ምላሽ መስጠት ጀመረ። ጄሬሚ ዶኩ እና ሴሜንዮ የሜዳውን ስፋት በመጠቀም የኒውካስል ተከላካዮች ወደ ኋላ እንዲያፈገፍጉ ያስገደዱ ሲሆን፣ ግብ ጠባቂው ኒክ ፖፕ ደግሞ የበርናርዶ ሲልቫ አደገኛ ኳስ ወደ ኤርሊንግ ሃላንድ ሳይደርስ ቀድሞ ለማዳን ተገዷል።

በአማካይ ክፍሉ ላይ ብዙ የጉልበት ፍልሚያዎች የታዩ ቢሆንም ከኳስ ውጪ በተፈጠረ ግጭት ጆሊንተን እና ኒኮ ኦሬይሊ ቢጫ ካርድ መመልከታቸውን ጨምሮ የመጀመሪያው አጋማሽ ያለ ግብ ተጠናቋል። በሁለቱም በኩል ያሉ ግብ ጠባቂዎችም ብዙም የተፈተኑበት አጋጣሚ አልነበረም።

ሴሜንዮ በድጋሚ ሲያስቆጥር ማንችስተር ሲቲ በኒውካስል ላይ የበላይነት አግኝቷል
https://www.reuters.com/resizer/v2/YYOULMTHB5KXTKFY4RFSLNMIXM.jpg?auth=7468aac4e2098d599672ef904e87414b75869c5d312bc2145397a7102c25cc69&width=1920&quality=80

ሴሜንዮ ልዩነቱን ፈጥሯል

ኒውካስል ከእረፍት መልስ በጠንካራ ሁኔታ የቀረበ ሲሆን ለግብም እጅግ ተቃርቦ ነበር፤ ዮአን ዊሳ በግንባሩ የገጨውን እና ወደ ግብ እየተንደረደረ የነበረውን ኳስ ጄምስ ትራፎርድ በሚገርም ብቃት ሲያወጣው፣ ከዛው የተመለሰውን ኳስ ብሩኖ ጊማሬሽ ቢመታውም የግቡ አግዳሚ መልሶበታል።

እነዚህን ዕድሎች ማባከን ዋጋ አስከፍሏል። ከሶስት ደቂቃ በኋላ ሲቲ ግብ አስቆጠረ። ሲልቫ ከዶኩ የተሻገረውን ኳስ በፍጥነት ለሴሜንዮ አመቻቸለት፤ ክንፍ ተጫዋቹም በተረጋጋ ሁኔታ በቅርብ ርቀት ከመረብ አሳርፎ ባለሜዳዎቹን መሪ አድርጓል።

ሴሜንዮ ከጥቂት ቆይታ በኋላ ከማዕዘን ምት የተሻገረውን ኳስ በመቆንጠጥ ሁለተኛ ግቡን ያስቆጠረ መስሎት ነበር፤ ነገር ግን ግቧ ከኤርሊንግ ሀላንድ ጋር በተያያዘ በነበረ ኦፍሳይድ ምክንያት ከረጅም ከቪኤአር ምርመራ በኋላ ውድቅ ሆናለች።

ቸርኪ የመጨረሻውን መርዶ አርድቷል

ኒውካስል አቻ የምትሆን ግብ ፍለጋ ወደ ፊት ቢገፋም፣ ሲቲ ግን በመረጋጋት ተከላክሏል። እንግዶቹ ሲቲዎች ጨዋታውን ገና በጠዋቱ ለመጨረስ ቢሞክሩም ኒክ ፖፕ ራያን ቸርኪን ሁለት ጊዜ መልሶበታል፤ ይሁን እንጂ ያ የናፈቁት ቅጽበት ተጨማሪ ሰዓት ላይ እውን ሆኗል።

ቸርኪ ከራያን አይት ኑሪ ጋር በመቀባበል ኳሷን በተረጋጋ ሁኔታ በኒክ ፖፕ አጠገብ አሳልፎ ከመረብ ጋር አገናኝቷታል። ይህም ውጤቱን 2 ለ 0 በማድረግ የስታዲየሙን ደጋፊ ጭጭ ከማድረጉም በላይ፣ ሲቲ በጨዋታው ላይ ያለውን የበላይነት ዳግም አረጋግጧል።

ሲቲዎች ግባቸውን ሳያስደፍሩ እና ሁለት ግብ ብልጫ  ይዘው ወደ ቤታቸው ሲመለሱ፣ ኒውካስሎች ግን በዚያ አስቆጭ ምሽት ያባከኗቸውን ዕድሎች እያሰቡ የሚቆጩበት ሆኖባቸዋል።

Related Articles

Back to top button