
በ10 ሰው ሰንደርላንድ በጠንካራ አቋሙ ቪላን አስደነገጠ።
አስቶን ቪላ በመጨረሻ በፕሪምየር ሊጉ ጎል ቢያስቆጥርም፣ በድጋሚ ቅር ተሰኝቶ ወጥቷል፤ ምክንያቱም 10 ሰው የቀረው
ሰንደርላንድ በጠንካራ አቋሙና በራስ መተማመኑ ተከላክሎ 1ለ1 አቻ መለያየት ችሏል።
የሰንደርላንድ የቅድመ-ጨዋታ እንቅፋት
አስር የሰንደርላንድ ተጫዋቾች በሜዳ ላይ ሲቀሩ የጨዋታው ሚዛን ወደ ቪላ አዘመመ። ሬይኒልዶ ማንዳቫንን ከማቲ ካሽ ጋር
በነበረው የጋለ ፍጥጫ ምክንያት በተሰራው ጥፋት ዳኛው ከሜዳ በቀይ አሰናብተውታል። ሰንደርላንድ በዚ ምክንያት ስልቱን
ለመቀየር ሲገደድ፣ ወጣቱ ክሪስ ሪግ የመጀመሪያ የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታው ተቋርጦ ተጨማሪ ተከላካይ ለማስገባት ተገደዋል።
የሰው እጥረት ቢኖርም ሰንደርላንድ ወደኋላ አላለም። ዊልሰን ኢሲዶር ከእረፍት በፊት ሁለት ጊዜ ወደ ጎል ቀርቦ የነበረ ሲሆን
አንዱን በኤዝሪ ኮንሳ የመከላከል እንቅስቃሴ ሌላውን ደግሞ ኢላማውን በሳተ ምት አምክኖታል።

የቪላ የአጥቂ መስመር ችግሮች
ለኡናይ ኤምሪ ቡድን፣ ነገሩ እንደቅርብ ሳምንታት ሁሉ ተመሳሳይ ነበር፡ ብዙ ኳስ ተቆጣጥሮ መጫወት ቢችሉም ውጤታማ
አልነበሩም። ኦሊ ዋትኪንስ ብቻውን ቀርቶ ሲበሳጭ የነበረ ሲሆን፣ ባገኘው ግማሽ ዕድልም ቢሆን ግብ ማስቆጠር አልቻለም።
ኢቫን ጉሳንድም ቢሆን በተገኘለት አጋጣሚ በቀጥታ ወደ ሰንደርላንድ ወጣት ግብ ጠባቂ ወደ ሮቢን ሮፍስ መቷል፣በአንፃሩ የ
ሰንደርላንድ ግብጠባቂ አሪፍ የሚባል የመጀመሪያ አጋማሽ አሳልፏል።
የቪላ ደጋፊዎች በአጥቂዎቹ ቅንጅት መጓደል ተጨንቀዋል፣ ሞርጋን ሮጀርስም ኳሶችን በትክክል ማቀበል አልቻለም።
የመጀመሪያዎቹ 45 ደቂቃዎች ሲጠናቀቁ ቪላ ሳይሆን ሰንደርላንድ የበለጠ አደገኛ ነበር የሚል ስሜት ነበር።
ካሽ ከርቀት መትቶ ጎል አስቆጠረ
አስገራሚው ግብ በመጨረሻ በ67ኛው ደቂቃ ላይ ካልተጠበቀው ተጫዋች ተቆጠረ። ማቲ ካሽ ከ25 ያርድ ርቀት ላይ የተምዘገዘገ
ኳስ ወደ ጎል የላከ ሲሆን ግብጠባቂው ሮፍስንን ግራ አጋባው። የሰንደርላንድ ግብ ጠባቂ የኳሷን አቅጣጫ ለመቀየር ሞክሮ ጣቶቹ
ነክተዋት ነበር፣ ነገር ግን ልያድናት አልቻለም። ቪላዎች በመጨረሻ በሊጉ የጎል እጦት ችግራቸውን በማብቃታቸው ተደስተው
አከበሩ።
ኢሲዶር የአቻዋን ግብ አስቆጠረ
ቪላዎች ጨዋታው ተጠናቋል ብለው ካሰቡ ተሳስተዋል። ሰንደርላንድ ከግራኒት ዣካ እና ከኤንዞ ለ ፌ መሃል ሜዳ በተቀናጀ ኃይል
ወደፊት ገፍተው ጨዋታውን መቆጣጠር ጀመሩ። ዣካ በጭንቅላቱ ወደ ኋላ መስመር በላካት ኳስ ጥረታቸው ፍሬ አፈራ።
ኢሲዶር ኳሷን በቮሊ አድርጎ ኤሚ ማርቲኔዝን በማለፍ ውጤቱን 1ለ1 አደረገ።
ይህ በሜዳው ባደረጋቸው ሶስት ጨዋታዎች ያስቆጠራት ሶስተኛ ግብ ነች። ይህም የሰንደርላንድ የሞራል ጥንካሬ ከጎደላቸው
የተጫዋቾች ቁጥር የበለጠ እንደሆነ ማረጋገጫ ነው።

ቪላ ያመከናቸው ተጨማሪ ዕድሎች
ሀርቪ ኤልዮት እና ኢያን ማትሰን የቪላን የጨዋታ ፍጥነት ለመጨመር ወደ ሜዳ ቢገቡም ያመጡት ለውጥ ውስን ነበር። ኤልዮት
ኢላማውን የሳተ ምት አድርጎ የነበረ ሲሆን ዋትኪንስ ደግሞ ከጄደን ሳንቾ ፍፁም የሆነ ኳስ አመቻችቶለትም ቢሆን ጎል
ማስቆጠር ባለመቻሉ የዕለቱን ድንቅ አጋጣሚ አምክኗል።
በሜዳው ዳርቻ ላይ የነበረው ኤምሪ ቡድኑ ሊያሸንፈው የሚችለውን ሌላ ጨዋታ እንዳመለጠው ያውቅ ነበር። ቪላ በዚህ
የውድድር ዘመን የመጀመሪያ ጎላቸውን አግኝተው ይሆናል፣ ግን የጠፋውን ስልታቸውን ማግኘት ግን ትልቁ ፈተና ሆኖባቸዋል።