ዌልቤክ ማንቸስተር ዩናይትድን አስለቀሰ፤ ብራይተን ታሪካዊ ድል ተቀዳጅቷል
ዩናይትድ በጊዜያዊ አሰልጣኝ መሪነት ከውድድሩ ውጭ ሆኗል
ውጥንቅጡ በወጣ የውድድር ዘመን ውስጥ የሚገኘው እና ያለ ቋሚ አሰልጣኝ የሚንቀሳቀሰው ማንቺስተር ዩናይትድ፣ ቢያንስ አንድ ዋንጫ በማንሳት ክብሩን ለማስመለስ የነበረው ተስፋ በቀድሞው የክለቡ ተወዳጅ ተጫዋች ዳኒ ዌልቤክ ተገትቷል። ብራይተን በኦልድ ትራፎርድ 2 ለ 1 በሆነ ውጤት በማሸነፍ በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ ዩናይትድን ከኤፍ ኤ ካፕ ውጭ ማድረግ ችሏል።
በሩበን አሞሪም መባረር የጀመረው ያ አስቸጋሪ እና ውጥረት የነገሰበት ሳምንት፣ በዩናይትድ ሽንፈት እና ከውድድሩ መሰናበት ተደምድሟል። ዳረን ፍሌቸር በጊዜያዊ አሰልጣኝነት በመሩት የመጨረሻ ጨዋታቸው ሊሆን በሚችለው በዚህ ፍልሚያ፣ ቡድኑ በሶስተኛው ዙር መሰናበቱ ተረጋግጧል።
ብራይተን የቆየውን የኤፍ ኤ ካፕ እርግማን ሰበረ
ብራይተን ቀደም ሲል በኤፍ ኤ ካፕ ከማንቺስተር ዩናይትድ ጋር ባደረጋቸው ስድስት ግንኙነቶች በሙሉ ተሸንፎ ከውድድሩ ቢሰናበትም፣ ያ መጥፎ ታሪክ ግን አሁን አብቅቷል። ይህም ሊሳካ የቻለው ገና በጅማሮው በብራያን ግሩዳ በተቆጠረች ግብ እና ዳኒ ዌልቤክ በልጅነት ክለቡ ላይ ባስቆጠረው ስምንተኛ ግቡ አማካኝነት ነው።
ምንም እንኳን ቤንጃሚን ሴስኮ በጨዋታው መገባደጃ ላይ ያስቆጠራት ግብ ለዩናይትድ ተስፋን ብታጭርም፣ አልቢዮኖች ግን ውጤቱን አስጠብቀው ወጥተዋል። በጨዋታው መዝጊያ ሰዓት ላይ ታዳጊው ተቀያሪ ተጫዋች ሺ ሌሲ በቀይ ካርድ ቢሰናበትባቸውም፣ ብራይተኖች ግን ሳይበገሩ ድላቸውን አረጋግጠዋል።

የግብ ጠባቂው ድንቅ ብቃት ጨዋታውን ቀይሯል
ዳረን ፍሌቸር ጨዋታው ከመጀመሩ በፊት በኦልድ ትራፎርድ ደጋፊዎች ዘንድ ደመቅ ያለ አቀባበል ተደርጎላቸዋል፤ ዩናይትድም ጨዋታውን በጥሩ መነሳሳት ነበር የጀመረው። ይሁን እንጂ የብራይተኑ ግብ ጠባቂ ጄሰን ስቲል ገና በጅማሮው ያደረጋቸው ሁለት ወሳኝ ኳሶችን የማዳን ብቃቶች የጨዋታውን ፍሰት የቀየሩ ሆነዋል።
የብራይተኑ ግብ ጠባቂ ገና በሁለተኛው ደቂቃ ላይ ከዲዮጎ ዳሎት የተሰነዘረውን ሙከራ ካከሸፈ በኋላ፣ ብራይተን ግብ ከማስቆጠሩ ጥቂት ቀደም ብሎ ደግሞ ብሩኖ ፈርናንዴዝ ከርቀት የሞከረውን ጠንካራ ኳስ መልሶበታል
ግሩዳ መሪነቱን አስገኝቷል
በዩናይትድ በኩል ታዳጊው ሺ ሌሲ እና ጆሹዋ ዚርክዚን በማስገባት የተጫዋቾች ለውጥ ቢደረግም፣ ብራይተኖች ግን ወዲያውኑ ነበር ሁለተኛ ግብ ያስቆጠሩት።
ብራያን ግሩዳ ያመቻቸለትን ቀላል ኳስ ዳኒ ዌልቤክ በግብ ክልል ውስጥ እጅግ ሰፊ ቦታ ተሰጥቶት ተቆጣጥሮታል። ዌልቤክም በ65ኛው ደቂቃ ላይ ድንቅ የሆነ አጨራረስ በማሳየት ኳሷን በግቡ የላይኛው የግራ ጥግ ላይ አሳርፏታል።
ከባለሜዳዎቹ በኩል የቀረበው ምላሽ ደካማ ነበር
ማንቺስተር ዩናይትድ ኳስን ተቆጣጥሮ የተጫወተባቸው ጊዜያት ቢኖሩም፣ ግልፅ የግብ ዕድሎችን ለመፍጠር ግን ተቸግሮ ነበር። በብሩኖ ፈርናንዴዝ ብልሀት የታከለበት የቅጣት ምት እና በማቴየስ ኩኛ ሙከራ ካልሆነ በስተቀር ተስፋ ሰጪ የሚባሉ እንቅስቃሴዎች አልታዩም። ከእረፍት በፊትም የኦልድ ትራፎርድ ድባብ እየቀዘቀዘ መጥቶ ነበር።
ዳረን ፍሌቸር ከእረፍት መልስ ደጋፊውን ለማነቃቃት ቢሞክሩም፣ ሁለተኛው አጋማሽ ግን ልክ እንደ መጀመሪያው ሁሉ ምንም አይነት ድምቀት በሌለው ሁኔታ ተጀምሯል።
ዌልቤክ የመጨረሻውን መርዶ አረዳ
በሁለተኛው አጋማሽ ፍሌቸር ተቀያሪ ተጫዋቾችን ሌሲ እና ዚርክዚ ቢያስገቡም፣ ብራይተን ግን ወዲያውኑ ሁለተኛ ግብ አግኝቷል። ግሩዳ ያመቻቸለትን ኳስ ዌልቤክ በጣም ሰፊ ቦታ ተሰጥቶት በ65ኛው ደቂቃ ላይ ድንቅ በሆነ አጨራረስ መረቡ ላይ አሳርፏታል።

የሴስኮ ግብ እና የቀይ ካርድ ድራማ
የዩናይትድ ደጋፊዎች ቡድናቸውን ወደ ፊት ቢገፋፉም፣ በ85ኛው ደቂቃ ላይ ሴስኮ በግንባሩ ካስቆጠራት ግብ ውጭ ሌላ ግብ ማግኘት አልቻሉም። ዩናይትድ አቻ ለመሆን ቢሞክርም ሳይሳካለት ቀርቷል፤ በምትኩ የ18 ዓመቱ ተቀያሪ ተጫዋች ሺ ሌሲ በሁለት ቢጫ ካርድ በቀይ ካርድ ከሜዳ ወጥቷል።
ለዩናይትድ ሌላው መጥፎ የታሪክ ምዕራፍ
ይህ ሽንፈት ከ1981-82 የውድድር ዘመን በኋላ ዩናይትድ በሁለቱም የሀገር ውስጥ ዋንጫዎች ኤፍ ኤ ካፕ እና ካራባኦ ካፕ በመጀመሪያው ዙር የተሰናበተበት የመጀመርያው አጋጣሚ ሆኖ ተመዝግቧል። በተጨማሪም ዩናይትድ በዚህ የውድድር ዘመን የሚያደርጋቸው ጠቅላላ ጨዋታዎች ብዛት 40 ብቻ መሆኑ የተረጋገጠ ሲሆን፣ ይህም ባለፉት 111 ዓመታት ውስጥ ክለቡ ያደረገው እጅግ ዝቅተኛው የጨዋታ ብዛት ነው።
አሁን ላይ ሙሉ ትኩረቱ በፕሪምየር ሊጉ ላይ ብቻ ለመሆን የተገደደው ዩናይትድ፣ ከመሪው አርሰናል ጋር ያለው የ17 ነጥብ ሰፊ ልዩነት ሲታከልበት፣ በዘንድሮው የውድድር ዘመን ዋንጫ የማንሳት እውነተኛ ተስፋው ገና በ2026 መጀመሪያ 11 ቀናት ውስጥ ተሟጥጦ አልቋል።


