
የ ቶትንሀም 2025/2026 የውድድር ዘመን ቅድመ እይታ
ቶትንሀሞች አምና ከነበራቸው አስከፊ የ 17 ኝነት ውጤት በኋላ እራሳቸውን ለማሻሻል እየሞከሩ ነው።ቡድኑ አዲሱን አሰልጣኝ
ቶማስ ፍራንክን ስኬትንና መረጋጋት ለቡድኑ ያመጣሉ ብሎ በማመን ቀጥሯል።ከዚህ ቀደም ፍራንክ ብሬንትፎርድን ያሰለጠነ ሲሆን
ቡድኑ ጥሩ እንዲጫወት እና ልምድ ማግኘትም ችሏል። አሁን ላይ ባገኘው የተሻለ ጥራት እና አቅርቦት የተነሳ ቶትነሀምን
ወደተሻለ ውጤት ይመራል ተብሎ ይጠበቃል።

አዲስ ፈራሚዎች እና የቡድን ለውጥ
ቡድኑን ለማጠንከር በማሰብ ቁልፍ ዝውውሮች የተደረጉ ሲሆን ሞሀመድ ቅዱስ ፣ ማትያስ ቴል እና ጆአዎ ፓሊኒሀ ቡድኑን
ተቀላቅለዋል። በተለይም ጆአዎ ፓሊኒሀ የቡድኑን የመሀል ክፍል ያጠናክራል ተብሎ ይጠበቃል። ሆኖም ቡድኑ የ ጀምስ ማዲሰንን
የጉልበት ጉዳት ጨምሮ የዚህን የውድድር ዘመን ጫና ዉስጥ ሊከቱ የሚችሉ ፈተናዎች እያጋጠሙት ነው።

ፈተናዎች እና ግምት
ባለፈው የውድድር አመት የ አውሮፓ ሊግ ዋንጫን ማሳካት ቢችልም በ ፕሪሚየር ሊጉ ግን ብዙ ፈተናዎችን ተጋፍጧዋል። የ
አምበላቸው ሰን ሆንግ ሚን ወደ ሎሳንጀለስ መሄድ ለቡድኑ የከፍታ ጊዜ እንደማብቂያ ይታያል። ቡድኑ የተሻለ ውጤት
ለማስመዝገብ እንዲችል ከነዚህ ለውጦች ጋር መላመድ እና ጠንክሮ መስራት ይጠበቅባቸዋል።
የውድድር አመቱ እይታ
በአዲሱ አሰልጣኝ እና ባስፈረሙት አዳዲስ ተጫዋቾች በመታገዝ የተሻለ ውጤት የማምጣት እድል ይኖራቸዋል። በደረጃው
ሰንጠረዥ መሀል ለመቀመጥ ማለም ለቡድኑ ጥሩ መሻሻል ይሆናል። የቡድኑ ውጤት ማማር በቡድኑ አባላት ለአዲሱ የአጨዋወት
መንገድ ቶሎ መላመድ እና በውድድር አመቱ መጀመሪያ ላይ የሚመጡትን ፈተናዎች ማለፍ ላይ ይወሰናል።

ትንበያ
አሁን ካለው ሁኔታ እና ፈተናዎች አንፃር ለ ቶትነሀም በዚህ የውድድር አመት 6ተኛ ደረጃ ላይ ሆኖ ማጠናቀቅ የሚቻል ይመስላል፤
ይህም ለክለቡ ቀጣይ ስኬት ታላቅ የሚባል መሰረትን የሚጥል ጥሩ መሻሻል ይሆናል።